+251 22 21 21 121, +251 22 21 22 692 Adama City, Melka Adama Sub-City, Abba Gada Oromia, Ethiopia
The First
Economic Zone in Ethiopia

በገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን(GSEZ) ባለስልጣንና በቻይናው ሲሲኢሲሲ(CCECC) መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

በገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ባለስልጣን እና የቻይና መንግስት ድርጅት በሆነው ሲሲኢሲሲ መካከል የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የጋራ ልማት የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፥ የጋራ ስምምነቱ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለስልጣን በሚያዘጋጀው 1 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሎጂስቲክስ ማዕከል፣ የኤክስፖርት ማቀነባበሪያ ማዕከል፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለአካባቢያዊ ነፃ ገበያ እና ለሌሎች የኢንቨስትመንት ልማት ለማዋል የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱም በኢትዮጵያ መንግስትና በቻይና መንግስት መካከል ያለውን የልማትና የኢንቨስትመንት ግንኙነትን መሰረት በማድረግ በቻይና የተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ አልሚዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲያለሙ በመሳብ ይህ የኢኮኖሚ ዞን “China Road and Belt Initiatives” አካል እንዲሆን እንደሚሰራም አመላክተዋል።

የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በዚህ ፕሮግራሙ ጥሪ ላይ ለመጡ እና ለሚመጡ አልሚዎች 2 ሺህ 900 ሄክታር መሬት ማዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

ባለስልጣኑ በ24 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በአዋጅ የተቋቋመ ሲሆን÷ እንደ ሀገር በአይነቱ የመጀመሪያው የኢኮኖሚ ዞን ነው።

admin
About the author

Leave a Reply

Total Visitor

020330
Views Today : 1571
Total views : 71709
Who's Online : 3